- የታክሲ ከሌለህ ወርደህ በባስ ሂድ
- ሠውን ማመን ተፈራርሞ ነው
- ፍቅር ካለ ባጃጅ ባስ ይሆናል
- በቴሌቶን ሂሳብ መክፈል ክልክል ነው
- ሒሳብ ሳይከፍሉ ሀሳብ አይጀምሩ
- ለፀባይኛ ተሳፋሪ የፀባይ ዋንጫ እንሸላማለን
- ለስራ ነው የወጣነው
- በመጀመሪያ የጋለ ደምህን ተቆጣጠርና ሀሳብህን ግለፅ
- ባለጌና ዋንጫ ከወደአፉ ይሠፋል
- ኤች.አይ.ቪንና የጫማ ሽታን በጋራ እንከላከል
- ማንችስተር ያሸንፋል አርሠናል ለዘለዓለም ይኑር
- ሠው አካውንት ይከፍታል አንዳንዱ አፉን ይከፍታል
- ሞባይል ለጣለ ሲም እንመልሳለን
- ሹፌሩን መጥበስ ክልክል ነው በነገር
- ሠው ብቻ ነው የምንጭነው በስህተት የገባ ይውረድ
- ታክሲ ለሚጠቀሙ ብቻ
- ክቡራን ተሳፋሪዎቻችን በአገልግሎት አሰጣጣችን ላይ አስተያየት፣ቅሬታ፣ትዝብት ወይም መሻሻል አለበት የምትሉት ነገር ካለ አንቀበልም!! መውረድ ይቻላል::
- ለሠው ቅን ሁን እንጂ ቅንቅን አትሁን
- ማስቲካ የሚታደል መስሎአችሁ አፋችሁን እንዳትከፍቱ
- መስኮቱን በመክፈት ለትራፊክ ፖሊስ አያጋፍጡን!
- ጤነኛ ካልሆኑ መውረጃዎ ደርሷል
- በጭነት መኪና መታችሁ እዚህ ትቀናጣላችሁ
- የክፍለ ከተማ ሠዎች ካላችሁ ሒሳብ በቅድሚያ
- ኑሮአችሁ ሳይሞላ "ታክሲው አልሞላም?! " ትላላችሁ!·
- ጥብቅ ማሳሰቢያ ለክቡራን ሌቦች ሒሳብ ሰብስበን ሳንጨርስ ስራችሁን መጀመር አትችሉም! የማይስማማ ሌባ ካለ መውረድ ይችላል
- ለዓለም ሙቀት መጨመር መንስዔው ጭቅጭቅ ነው
- ይህ ታፔላ የሚሉት ከመጣ ፤ ምሳችን በቆሎ ራታችን ቂጣ
- ታክሲው ሳይቆም መውረድ ይቻላል
- እንዴት ጭት አትቃሙ ይባላል፣ ሰርቶ የማይዝናና አህያ ብቻ ነው
- የበታችነት ከተሰማህ ዛፍ ላይ ውጣ
- ስልጣን ህዝብን ማገልገያ እንጂ ማስፈራሪያ አይደለም
- የቤትህን አመል እዛው!!!
- የሠው ትርፍ የለውም . . . ተጠጋጉ!
- በታክሲ. . . . . ህግ አላውቅም
- ታክሲና መንግስተ ሰማያት ሞልቶ አያውቅም
- ለታላቅ መልስ አይሰጥም
- ነገን ለመኖር መጀመሪያ ዛሬን ኑር..በመቃም
- ‹‹ደሀ›› ከፍ ብሎ የሚታየው ባስ ላይ እና እራሱን ሲሰቅል ብቻ ነው፡፡
- እባክዎን የአባይ ቃል ስላለብን ጠጋ ጠጋ ይበሉልን
- ለካፌና ለላዳ ብዙ ይከፍላሉ፤ እኛ ጋ ሲሳፈሩ ለምን ይጨቃጨቃሉ
Tuesday, June 4, 2013
Subscribe to:
Comments (Atom)